የልጅነት ጉዳቱን ያላከመ ቤተሰብ የጠቅላላ ግንዛቤው፣ አመለካከቱ የአይምሮውን ጥልቅ ትክክላኛ ስሜቶችን ያንጸባርቀዋል።


በወላጆች መሀልም፣

  • በቤተሰቦች ውስጥ በአንድ ቤት ውስጥ አብረው በሚኖሩ፣ በጥም ብዙ የሚያጋጥሙ ችግሮች፣ የአመለካከት እና የሀሳቦች መጋጨት፣ የመሰረታዊ የሆኑ እና ያልሆኑ የአቋም ልዩነቶች መፈጠር፣ሌላም ብዙ የማያግባቡ ችግሮች በመሀል ሊፈጠሩ ይችላሉ

  • ችግሩ ሲከሰት ግን የግለሰቡ የአይምሮ ጤና የግለሰቡን ችግሩን ለመፍታት፣ የመቋቋም፣ለመቀበል ወይም ለማስተናገድ የአይምሮው ጊዜአዊው ጤናው ይወስነዋል። ለሁሉም ሰላማዊ እና ጤናማ የህይወት እትምጃዎች መጀመሪያ ጥሩ የአእምሮ ጤናን ለመያዝ ይጠይቃል። 

  • የራስን አመለካከት ለማሻሻል እና ስሜታዊ ሰላምን ለማግኘት፣ውስጣዊውን፣ ከልጅነት የህልና ጠባሳ ካለው አክሞ፣ ውስጣዊ የስሜት ሰላምን ማግኘት በመጀመሪያ ያስፈልጋል።

  • በተለያየ አጋጣሚ፣ ሁላችንም በዚህ ምድር ላይ የምንኖር ሰዎች ሁሉ፣ የአይምሮ (የጸባይ) ውስጣዊ የሆነ በቀላሉ ለኛ ሊታይ ወያም ልንረዳው የማንችለው ግን በስነ ልቦና ሀኪሞች የሚረዳና ሊታከም የሚችል የስሜታችንን ሞተር ማዛባት ሀይል ያለው ካላወቅነው ህይወታችንን የሚያዘበራርቅ ጥልቅ ጠባሳ ሊያጋጥመን መቻሉ እርግጥ የሆነ ነገር ነው። 

ነገር ግን ለራሳችን አመል፣ ጸባይና፣የአይምሮ ጤና በነገሮች ላይ ያለንን አመለካከት፣  በየጊዜው እየገመገምን ከቀን ወደ ቀን በማረም የምናሻሽል እናም የምናሳድግ ለመሆን ፍቃደኛ ሰዎች ከሆንን ጠባሳችንን አክመነዋል ማለት ነው። የህይወት ችግሮችም ካጋጠሙን ወዲያው ሳንፈራ ተጋፍጥንው መፍትሄ መፈለን ለመጀመር 

  • በቤተሰብ መሃል ያለመግባባትም ሆነ ሌላ አይነት ችግሮች ሲያጋጥሙን ሸፋፍኖ ማሳለፍ ፈጽሞ መልካም ለውጥን አያመጣልንም። ግን ነገሩን ወዲያው ተጋፍጦ መፍትሄ ማምጣት ይቻላል። የመጀመሪያው መሳሪያ ችግሩን እኔ ነኝ ብሎ መቀበል ሌላውን የቤተሰብ አባልም በዚሁ መልክ ለችግሩ ጥናትን እንዲያደርግ ይጋብዘዋል። 

  • ይህንን ሂደት በቀላሉ ማድረግ ከተሳነን ግን ስር የሰደደ ውስጥዊ ቁሥል ሊኖረን ስለሚችል የተደበቀ ቁስላችንን እያዳመጥን ከሆነ፣የምናረገውን ለመረዳትና የቆየ ውስጣዊ~ጠባሳን አክሞ ለማዳን ስራን ለመጀመር መወሰን እና ያለማወዳደቅ ወደ መፍትሄው ለመግባት በግልጽነትና በመከባበር ከቤተሰብ ጋራ አብሮ መስራት ተገቢ ነው።

  • የግልንም ሆነ የቤተሰባችንን አይምሮአዊ ሰላም፣ ጤና ለመጠበቅ ከራሳችን መጀመር ግድ ነው። በተለይም በባህላዊና ሃይማኖታዊ የቤተሰብ አወቃቀሮች ውስጥ፣ በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ የቤተሰብ አባላቶች፣ ጤናማ ፣ እምነት፣እና የቤተሰብ መከባበርን የሰፈነበትን ቤተሰብ ለመገንባት፣ የቤቱ አስተዳዳሪ ለሁሉም አባላቶች ፍቅርን፤ እና፣ ሰላምን መሰረታቸው በማረግ ቤቱን ማስተዳደር ጥቅሙን የማያልቅ ያረግላቸዋል።

  • የቤት አስተዳዳሪዎች ሁሉንም የቤተሰባቸውን አባላት ያለማዳላትና ያለማበላለጥ አክብሮታዊ መንፈስን በተላበሰ በግልጽነት ቤተሰብን መምራት ወሳኝ ነው። የሚተማመን ቤተሰብ ውስጥ መኖር በህይወት የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ያቀላል፣ በቤተሰባዊንት መተጋገዝ ለችግሮችም ወዲያው መፍትሄውን ለማምጣት በጣም ይቀላል። የመንፈስንም ሆነ የአይምሮ ጭንቅቶችን ከቤተሰቡ ያርቃል፣ በአንድ በቤተሰብ መሃል መተማመን እርስ በርስ ለመመካት ያስችላል። በአንዱምላይ የአይምሮ ወይም ሌላ አይነት  ችግር ቢያጋጥም  ምንም ሳይሰጉ በመተማመን  ለቤተስብ በግልጽ ተማክረው ችግሩን በቶሎ ለመፍታት እድልን ይፈጥራል።

  • ባአንድ ቤት ስር የሚኖር በቤተሰብ ለሚያጋጥመው የአይምሮአዊ ጭንቅት (ችግር፣ ህመም) በግልጽ መነጋገር በቶሎ ወደ ተሻለ ጤናማ አይምሮ ክልል ውስጥ ለመመለስ ይረዳል።

ለሁሉም ጥሩ ነገር የግል ፍቃደኝነት መኖር ወሳኝነት አለው፡ 

  • የግልን አመለካከት አስተውሎ መረዳት፡ ከሁሉም በፊት በራስ አመል ላይ በቅድሚያ ለመስራት ፍጹም ፍቃደኛ መሆን፡ ለቤተሰብ አስተዳዳሪ የመጀመሪያ የኑሮ ማቅለያ መሳሪያ ነው ይህ ግን ቀላል የሚሆነው የቤተሰቡ መሪ ሙሉ የተስተካከለ የአይምሮ ደህንነት ይዞ ህይወትን የሚመራ ግለሰብ ሲሆን ብቻ ነው። 

  • በልጅነት ወቅት ያጋጠመውን የአይምሮ ጥልቅ ድብቅ ጠባሳ አክሞ ያዳነ ግለሰብ፣ ወይም ቋሚ ያልታከመ ህመም የማያሰቃየው አይምሮን የያዘ ግለሰብ፣ ባጭሩ ጤነኛ ጭንቅላት ያለው ግለሰብ ተግባሩን ሁሉ እየገመገመ ራሱን ተመልክቶ ጥፋቱን ሲያገኝ ፣ያለውርዴታዊ ስሜቶች ትጽእኖ ጥፋቱን በጸጋ አምኖ ወዲያው ማረም እንደ ስኬት ያይዋል ብዙ ግዜም ደጋግሞ ተመሳሳይ ጥፋትን ላለመስራት ይበቃል፣ በሌላ መልኩ ሰዎች ውስጣዊ የማይረዱት እና ጥቂቶች ተረድትው ሳያክሙት ችላ ያሉት ጎጂ ጥልቅ ስሜታዊ ጠባሳቸው የጊዜአዊውን ገጠማቸውን እያታለሉ መሆኑም ቢረዱትም ጥፋታቸው በሌሎች አይን አለመታያቱ እጅግ በጣም ያስደስታቸዋል። 

ይህ የሚሆነው ካላቸው ፍራቻ እና በልጅእነታቸው ካደረባቸው ድብቅና ሃይለኛ የሆነ በራስ ያለመተማመን ስሜቶች እንደሆኑ በብዙ የስነልቦናዊ ጥልቅ ምርምሮች ተረጋግጥዋል።  በተለያየ ደረጃ እና ምክያት ሁላችንም በጥልቅአዊ የልጅነት ቁስል ስሜታችን ውስጥ ተቀብሮ ይሆናል፣ ያ ሰው ምን ይለኛል፣ ሰው ይተወኛል፣ የሚል ፍራቻ ደረጃው ከሰው ሰው ይለያያል ግን ታውቆ ካልታከመ ትዳር ሲጀመር ወላጅነት ሲመጣ  ያ ችላ ብለን ደባብቀን የኖርነው ይልጅነት እሞሽናል ጠባሳ ካለብን አፍጦ ይመጣና ቤተሰብን ሙሉ ይጎዳል።

  • እንደኔ ጥናትና ግንዛቤ ከልጅነት የመንፈስ ቁስል ማምለጥ በዚህ አለም አይቻልም ግን ቁስሉን በትክክል ከአይምሮ ባለሞያዎች እርዳታ በመስራት ለማግኘትና የሚሰጡትን ምክር በመጠቀም ድሮ የተደበቀው የስሜት ቁስል  ( “Emotional core wounds”) የአሁኑን ህይወቱን እንዳያጨልመው ለማድረግ ይቻላል።

የተደበቀም ሆነ የሚታይ በልጅነት ቁስል ምክንያት የሚፈጥሩ የጸባይ መዛባቶች፣ ከቅርብ ቤተሰቡ ጋራ ብጣም ትንሽ የሆነ ግጭት ሲያጋጥመው፣ የሚቆጣጠረው የአይምሮ ክፍሉ ሳይሆን ቁስሉን ደብቅ የያዘው የአየምሮው አካል ስለሚሆን ውስጣዊ ጠባሳው ገናና ይሆንእና የግለሰቡን ስሜት ግለሰቡንም ቤተሰቡንም ያለማቋረጥ ያለምንም መሻሻል ይብጠብጣቸዋ። (Subconscious trauma always powerful  can easily react to distressing experiences with loved ones because it stored in the unconscious mind, it is just creating hidden patterns that affect the person's life) ምክያቱም ያ ህመሙን በአይምሮ ህክምና ያላዳነ ግለሰብ የድሮው ጠባሳ ስሜቶቹ መጥተው የአሁኑን መልካም ነገሩን ሁሉ በመረበሽ የስሜቱን ሰላም በህመም ይቆጣጠሩበታል፣ በዚህም የተነሳ  ዐንድ ግለሰብ የራሱን ህመም ቀድሞ ከማከም፣ ወይም ጥፋቱን ከማስተካከል ይልቅ በሌሎች ላይ እየፈረደ፣ በተለያየ መልኩ በመደባደብ፣ በመሳደብ፣ በማሸማቀቅ፣ በጣም የቅርባቸውን ሰዎችን ስሜታቸውን በጫን እና ጠልቆ በሚሰማ መልኩ እነሱ ድሮ በልጅነታቸው ዘመን ሊንከባከባቸው የሚገባው ሰው ከጎዳቸው በላይ ሌሎችን ሲጎዱ ይታያሉ። ቀስ በቀስም ሌሎችን እየበደሉ እየጎዱ መኞርን እንደ ደስታ ማመንጫ መሳሪያ ያረጉታል። 

እንደዚህ አይነቱ የጸባይ ጉድለት መቃወስ እጅግ ብሁ አይንት መልኮች አሏቸው። ሆንው እያንዳንዳቸው የጸባይም ሆነ የአይምሮ ጤና መሰናክሎች የጥንካሪያቸው እና ደረጃቸው ከሰው ስው በየእያንዳንዱ ሰው ላይ የሚያስከትሉት ተጽኖቸውም ይለያያሉ። 

የአይምሮ ጤና መቃወስን እና የባህሪ ችግሮችን ወደልጆች እንዳያልፍ ማቆም፡

  • በቤተሰብ መሀል ቋሚ ግጭትን የስሜት መሰቃየትን ልምድ ማድረግ፡ በይበልጥ ችግሮቹ እየተስፋፋና ትውልዳዊ ሆኖ ልማድ የሚሆንን ቀጣይነት ያለው ጉዳትን ያመጣል።

  • አዋቂዎች፣ ግለሰቡ የአይምሮውን ችግር ጸባዩን ወደ መልካም ጸባይ ለማደስ፣ ከልጅነታቸው ጀምሮ ያስቸገራቸውን ነገር አምነውበት እርዳታን ለራሳቸው ካልተጠቀሙ፣ ወይም ሸፋፍነው ለማዳን  ሳይፈቅዱ ወደ ፍቅር ወይም ወደ ትዳር ግንኙነት ሲገቡ ያድብቅ ጎጂ የጸባይ ሁሉ በግልጽ መውጣትና የህይወታቸውን፣ አጋራቸውን፣ በግልጭ መጉዳት ይቀጥላል። የራስንም ሰላም ማጣትን  ልምድ እያረጉት ይመጣሉ። 

  • የትዳር ክፍሉ የቀን በቀን ጭቅጭቅ ነው ብሎ መቀበል ከራስም አልፎ በልጆቻችን ህወት ላይ መፍረድ ይሆናል። 

  • በጋብቻው ውስጥ ያሉት ጥንዶች ተመሳሳይ የጸባይ ችግር እና የህሌና ቁስላቸው መሰረተ ምክያት ሆኖ ካጣመራቸው (A“Trauma bond love” connections and the emotional attachments) እነዚህ ጥንዶች በግንኙነታቸው ላይ ሁሉ ተደጋጋሚ ወይም ቋሚ መጥፎ ጸባዮች ቢኖርም አይምሮዋቸው  የተላመደው ስቃይ ስለሚሆን፣ ቢጎዳም መታመሙን ሳይሰማቸው ቀስበቀስ ሲብስበት ጭንቅላታቸው ስራውን አቁሞ እንደ ማሽን እራሱን ከህመም የሚያሳርፍበትን አቋራጭ መንገድ ሊወስድ ይችላል። ይሄ የአይምሮ እርምጃ ሳይደርስ ሰዎች ሰላማቸውን መፍጠር ያስፈልጋቸዋል።

  • የአይምሮን ጉዳት ለረጅም ጊዜ ሳያክሙ መቆየት እጅግ ከባድ አደጋ አለው። ከትልቅ ችሮች ትግል በኋላ ጭንቅላታችን ለማሳረፍ እና ያለምንም ውጫዊ መጠጥም ሆነ ሱስ ነክ ነገሮችን ባለመጠቀም ፣አይምሮአችን በተፈጥሮው የሚያሰራጨውን ሆርሞን ብቻ ተጥቅመው እንዲጠገኑ የተዛቡት ሆርሞኖች ስራቸውን በትክክል እንዲቀጥሉ ለመጠገን እንዲችሉ በቂ ሰላማዊ ግዜ (የመጠገኛ ጊዜ) መስጠት ከገቢው በላይ አስፈላጊ ነው። ይህ ለጤነኛ እና የአይምሮ የታወቅ ችግር ለሌላቸው፣ እና ፣ውስጣዊ ጠባሳቸውን ለታከመ አይምሮ ሲሆን፣

  • ነገር ግን ከልጅ እድሜያቸው ጀምሮ የታወቀ እና መቁጥጥር ስር የዋለት፣ እንዲሁም አይምሮ የአሰራር ገደብ ይዘው የተፈጠሩ ግለሰቦች ያለባቸው ግን ልዩ የሆነ ገደብ የበለጠ ተጎጂ ሊያረጋቸው ስለሚችል ትኩረት እና ተጨማሪ ሰላማዊ ዘላቂ ቤት ውስጥ በእንክብካቤ እና በተጨማሪ ቋሚ በሆነ ጥንቃቄ ይፈልጋሉ።  

  • በቤት ውስጥ ወይም በትዳር ውስጥ ግጭትን እንደ ህይወት ጸጋ በመቀበል ለጸባያቸው ለውስጣዊ ሰላማቸው የመሻሻልን ስራ ሳይሰሩ፣ ቀለል አርጎ በማየት፣ ትኩረት ሳይሰጡት ቀስ በቀስ ወደ ባሰና ወደ ከፋ ደረጃ፣ መፍትሄ አልባ፣ የጉዳት ላይ እስከሚደርሱ፣ በራሳቸው የአይምሮ ጤና ላይ መስራትን  ያላጠናከሩ፣ህመማቸውን በሱስ ደብቅው የሚቆዩ፣ ግን በብዙ ፈተና ውስጥ የሚያልፉ፣  ከራሳቸው የሚመነጨውን የህሊና ሰላም ማጣት ለእረጅም ግዜ ላይረዱትም ይችላሉ።  እራስን ውስጣዊ ጭንቀት በሱስ መደንዘዝ ቶሎ ካልቆመ አይምሮ በተፈጥሮው እያመነጨ የሚያስተላልፈውን እና የሚያሰራጨውንም ጠቃሚ እና ለደህንነት ወሳኝ የሆኑትን የብሬን ሆርሞኖችም ወይም (Brain chemicals)በተገቢው ሁኔታ ማምረቱን እና በተገቢውም የሰውነት ስፍራዎች ማመላለሱን/ ማድረሱንም/ እያቆመ ይመጣል።

  • ሁሌም ችግር ያለባቸው ጥንዶች፣ ግዜን ሳያባክኑ፣ ጥሩና የሚረዳቸውን፣ ስለቤተሰብ ችግር ፈችነት ጥልቅ እውቀት ያለውን የስነ ልቦና፣ወይም የባህሪ አማካሪን የእርዳታ አገልግሎት፣ እገዛን መቀበል ያስፈልጋቸዋል።  እለታዊ የማያቋርጥ አደጋ ያለበት ቤት ችግሩን ለመፍታት ቅድሚያ መስጠት ቤተሰቡን ከከፋ ጠባሳ ጋራ ተያይዞ ከመፍረስ ያድነዋል፣ የልጆችንም ከቀጣይ የአይምሮ ጠባሳን ከመስጥት ይጠብቃል። እባካችሁ የቤታችሁን ሰላም ለመፍጠር አማካሪን ማየት እንደ ነውር አትቁጠሩት መካሪም መካሪ ያስፈልገዋል። ለምትወዱት ቤተሰብ እራሳችሁን ጤናማ በማረግ ጠብቁት። 

ጭቅጭቅ እና ፉክክር የሞላበት ትዳር፣ በልጆች የአይምሮ ጤና ላይ የእድገት ችግሮችን፣ ተደባቂ እናም በግልጽ የሚታዩንን፣ ተቀያያሪ የሆኑ ለወደፊት ህይወታቸው አሰናኳይ ሆነው የሚወጡ የተለያዩ የአይምሮ ችግሮች ይፈጥሩባቸዋል።  ለምን በዚህ ግዜ? የተጽኖውን ክብደት በልጆች ላይ የሚያሳድረውን ጭንቀት ውጤት ወደፊት በዝርዝር በጥልቅ ላቀርብላችሁ እሞክራለሁ። 

ፍቅር ሰላም ከሁላችሁ ጋራ ይሁን።

ኤሚ በላይ ዘለቀ።


Previous
Previous

የሐበሻ ስደተኛ ቤተሰቦች እና የልጆች የአእምሮ ጤና:

Next
Next

Fostering an Open Mindset Within a Traditional Family.