የሐበሻ ስደተኛ ቤተሰቦች እና የልጆች የአእምሮ ጤና:
ለወላጆች የሚሆን መልዕክት (Message for Parents)
የልጆቻችን ባህሪ ድንገት መለወጥ፣ ያልተለመደ ጸባይን ስናይባቸው፣ የግድ የክፋት ወይም የዐመፅ ውጤት ላይሆን ይችላል። ውስጣቸውን እያረበሻቸው ያለ ችግር ወይም ጭንቀት ሊሆን ስለሚችል ግዜ ሰጥተን ችግሩን እስከምንረዳ በትእግስት ያለ ግላዊ ድምዳሜ እራሳቸው የሚነግሩንን መከታተል እና በተለይ በደንብ የሚሉንን ሳናስደነግጥቸው ማዳምጥ እና መረዳት። መፍትሄውን ከመንገራችንም በፌት በማመስገንን እን አለሁላችሁ በማለት መጀመር። ለሁሉም እድሜ ላይ ላሉ ልጆች እምንትን እንዲጥሉብን ያረጋቸዋል።
ስሜታችንን መቆጣጠር እነሱንም ማዳመጥ እና፣ በስነስራት መወያየትን ካልፈቀድንላቸው፣ ከኛ ጋር የሚኖሩት ህይውትን እንድ እስርቤት ሊመለከቱት ይችላሉ። ለአይምሮ ጤናቸውም ብዙ ጊዜ የማያክሙት እና የሚጥራቀም ጭንቀት ወይም የውስጥ ስቃይ ወደ ውስጥቸው ሊቀረጽ ይችላል። እንዲህ አይነቱም ቤተስብ ግንኙነት ልጆችን ወድ ተስፋ መቁረጥ፣ መጥፎ ልማዶችም ሊመራቸው ይችላል ከእነዚህም አንዱ የተለመድው መጠጥ እና የአደንዛዥ እጽ ነው። ከልጆቻችን ጋር በግልጽ በተለይም በሰላም በመነጋገር እናም ያካልተቻለ ወደ ባለሙያ እርዳታ በመፈለግ ቤተሰባችንን ማዳን ልጆቻችንን መታደግ በደንብ እንችላለን።
(Habeshian Migrant Families and Children’s Mental Health)
በአዲስ ሀገር መኞር ስንጀምር፣ ልጆችን ማሳደግ በጣም ከፍተኛ ጥረት የሚጠይቅ ስራ ነው፣ ሁሌም በልባችን ማስቀመጥ ያለበን፣ ልጆቻችንም ያለኛ ማንም የላቸውም። በትምህርት ቤታቸው ውስጥና በሁለቱ ሀገሮቻ ቸው የበሀል ልዩንት ብቻ ቀን በቀን በልጅነት አይምሮቸው አቅም ብዙየሚታገሉት ትግል የሚያሳድርባቸውን የህሊና መወዛገብ እያጤንን መርዳትና በትግስት መቀበል ያለብን ብዙ ነገር ነው። ለእድሜያቸው በጣም የበዛ ችግርን ከእኛ ውጪ ሳንረዳቸው ንደሚያሳልፉ እረስተን እኛ ለእነሱ የምኛደርገውን ብቻ ለክተን ማየት የለብንም። ለልጆቻችን መመኪያቸው እኛ ብቻ ነን ብሎ መቀበል እጅግ በጣም ይረዳል።ዋናዎቹ ዋስትናቸው እኛ መሆናችንን ሁሌም ያልታሰበ ችግር በልጆቻችሁ ምክያት ሲያጋጥማችሁ አስታውሱት።
ብዙ ጊዜ በመጀመሪያው ስደተኛ ወላጅ፣ 1ኛው የሐበሻ ስደተኛ ቤተሰቦች ዘንድ በልጆች የአእምሮ ጤና ችግሮች እና በአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም መካከል ያለውን ልዩነት የመረዳት ክፍተት ይታያል። ይህ ደግሞ በቤተሰብ ውስጥ አለመግባባትን እና መገለልን (stigma) ይፈጥራል።
በአደንዛዥ ዕፅ እና በአእምሮ ጤና መካከል ያለው ግንኙነት
ምክንያት ወይስ ምልክት? ብዙ ጊዜ ልጆች በውስጣቸው ያለውን ጭንቀት ወይም ድብርት (Depression) መቋቋም ሲያቅታቸው፣ ህመማቸውን ለማስታገስ ወደ ተሳሳቱ ነገሮች ሊሳቡ ይችላሉ። ስለዚህ አደንዛዥ ዕፅ የችግሩ "መንስኤ" ብቻ ሳይሆን የውስጥ ስቃይ "ምልክት" ሊሆን እንደሚችል መረዳት አለብን።
ሁኔታውን መረዳት፦ የአእምሮ ጤና እንደ ማንኛውም የሰውነት በሽታ በጄኔቲክስ፣ በአካባቢያዊ ጫና እና በስነ-ልቦና ሊመጣ ይችላል። ይህን ማወቅ ለልጆቻችን ተገቢውን ድጋፍ እንድንሰጥ ይረዳናል።
እርዳታ ማግኘት እና መረዳዳት
መሰናክሎችን ማለፍ፦ መረጃ በማጣት ወይም በገንዘብ እጥረት ምክንያት ወደ ባለሙያ ላንሄድ እንችላለን። ነገር ግን የልጆቻችን ህይወት ከሁሉ በላይ ዋጋ አለው።
የመማር አስፈላጊነት፦ ስለ አእምሮ ጤና እውቀት ሲኖረን፣ ልጆቻችንን የመርዳት አቅማችን ይጨምራል።
የማህበረሰባችን ድጋፍ፦ በቤተክርስቲያን፣ በመስጊድ እና በተለያዩ የሀገር ልጆች ስብስቦች ውስጥ እርስ በእርስ መደጋገፍ እና መረጃ መለዋወጥ ለውጥ ያመጣል።
ለተሻለ ለውጥ ምን እናድርግ?
ግንዛቤን መፍጠር፦ ስለ አእምሮ ጤና በሰፊው እንነጋገር፤ ይህም በማህበረሰባችን ውስጥ ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ይቀንሳል።
በግልጽ መወያየት፦ ልጆቻችን ሳይፈሩ የውስጣቸውን እንዲነግሩን የፍቅር እና የሰላም ድባብ እንፍጠርላቸው።
አብሮ መስራት፦ ከአእምሮ ጤና ባለሙያዎች እና ከማህበረሰብ መሪዎች ጋር በመተባበር ለልጆቻችን አስተማማኝ ከለላ እንሁን።
ዋና ዋና ነጥቦች (Key Points):
ግንኙነቱን መረዳት፦ በልጆች የአእምሮ ጤና እና በአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም መካከል ያለውን ውስብስብ ግንኙነት መረዳት ለተሻለ ውጤት አስፈላጊ ነው።
ግንዛቤን ማሳደግ፦ ስለ አእምሮ ጤና ትክክለኛ ግንዛቤ በመፍጠር፣ በቤተሰብ ውስጥ ግልጽ ውይይትን ማበረታታት ይገባል።
የድጋፍ ስርዓቶችን ማቀናጀት፦ ቤተሰቦች የአእምሮ ጤና ተግባሮችን በብቃት እንዲወጡ ለማገዝ የተቀናጀ የባለሙያ እና የማህበረሰብ ድጋፍ ያስፈልጋል።
ቁልፍ ቃላት ትርጉም (Key Vocabulary)
Mental Health የአእምሮ ጤና (Ye'Aemiro Tena)
Drug Use የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም (Ye'Adenzaz Etz Ateka'kem)
Stigma / Shame መገለል ወይም ስድብ/ነውር (Megelel / Newur)
Awareness ግንዛቤ (Ginzabe)
Open Dialogue ግልጽ ውይይት (Giltz Wuyiyit)
Support System የድጋፍ ስርዓት (Ye'Digaf Sir'at)