ለሁሉም ቤት ሀላፊ፣ የቤተሰብ ግጭት አፈታትን መረዳት (Understanding Family Conflict Resolution)
የዚህ አጭር መረጃ ዋና ዓላማ የቤተሰቦችን አስፈላጊ በሆኑ የክህሎት መሣሪያዎች ማብቃት ነው።
የቤተሰብ ተደጋጋሚ ግጭቶችን አፈታት አቅም (ችሎታ) አስፈላጊነት፡
የቤተሰብ ግጭቶች የማንኛውም ግንኙነት ተፈጥሯዊ አካል ናቸው ማለት ይቻላል፣ ነገር ግን በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ከሆነ ወደ ጥልቅ ችግሮች ሊያመሩ ይችላሉ። ጤናማ የቤተሰብ ግንኙነትን ለመገንባት የእነዚህን ግጭቶች መነሻ መንስኤ መረዳት ወሳኝ ነው።
ተደጋጋሚ ሁኔታዎችን መለየት (Recognizing the Conflicts Patterns)
ተደጋጋሚ ችግሮችን መለየት (ተረድቶ ማስተዋል) መጀመር ያለበት ከራስ ነው የሌላውን የቤተሰብ አባል ለማየት የራስ ደህንነት ስለሚቀድምው ነው። ይህም ቤተሰቦች መፍትሔ የሚያስፈልጋቸው ዋና ዋና ችግሮችን እንዲረዱ ይረዳቸዋል።
ጠንካራ ግንኙነቶችን መገንባት
ግጭቶችን ውጤታማ በሆነ መንገድ በመፍታት፣
ቤተሰቦች ትስስራቸውን ማጠናከር
እና አጠቃላይ የሐሳብ ልውውጥን በየግዜው ማሻሻል ይችላሉ።
ለውጤታማ ግንኙነት የሚረዱ ዘዴዎች (Tools for Effective Communication)
በቤተሰብ ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ግልጽ ውይይቶች ወሳኝ ናቸው። እያንዳንዱ ሰው የሚደመጥበት (ክብር /መረዳዳት) ሰላማዊ የማያስፈራራ ቤተሰባዊ ቤት/ አካባቢ/ መፍጠር ግስጽ እና ቀጥተኛ የሐሳብ ልውውጥን ያበረታታል።
በቤት ውስጥ የሚደረግ ግልጽ ውይይት የቤተሰብ አባላት ስሜታቸውን እንዲገልጹ ስለሚረዳ፣ የስሜታዊ መረበሽን ውስጣዊ መጨነቅን በመቀነስ ስሜታዊ አለመረጋጋትን ይቀንሳል።
በጥንቃቄ ማዳመጥ (Active Listening): ይህ ማለት ሌሎች የሚሉትን ነገር ሳያቋርጡ ወይም መልስ ለመስጠት አስቀድመው ሳይዘጋጁ በትኩረት መስማትን ያካትታል።
ስሜትን መግለጽ: የቤተሰብ አባላት ስሜታቸውን በግልጽ እና በሐቀኝነት እንዲያጋሩ መበረታታት አለባቸው፤ ይህም በመካከላቸው የተሻለ መረዳዳት እና የድጋፍ ሥርዓት እንዲኖር ያደርጋል።
ያለ ፍርሃት ስሜታዊ አለመረጋጋትን መጋፈጥ: እነዚህ ውይይቶች ግለሰቡ የራሱን ችግር እንዲረዳ እና በቤተሰብ የድጋፍ ዕቅድ ውስጥ እንዲሳተፍ ይረዳሉ።
እያንዳንዱ ቤተሰብ እንደ ግለሰቡ ምርጫ የሚስማሙ የባህሪ ለውጦችን መለያ ዘዴዎችን ማዘጋጀት ይችላል። ለዚህም ግለሰቡ በፈቃደኝነት መሳተፍ ይኖርበታል።
ሁሉም የቤተሰብ አባላት ያለ ምንም ፍርድ ወይም ትችት ሐሳባቸውን የሚያጋሩበት ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ (የቤተሰብ ቤት) መፍጠር እጅግ አስፈላጊ ነው። ውጤታማ እንዲሆንም ቤተሰቡ መደበኛ የክትትል ጊዜያት ሊኖሩት ይገባል።
የ“እኔ” መግለጫዎችን መጠቀም (Utilizing “I” statements)
ስሜታዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የቤተሰብ አባላት ወደ ጤናማ ሁኔታ ለመመለስ፣ ቤተሰቡ በ "እኔ" የሚጀምሩ ንግግሮችን እንዲጠቀሙ ማበረታታት አለበት። ለምሳሌ፦
"እኔ ዛሬ ደህና አይሰማኝም"
"እኔ እርዳታ እፈልጋለሁ"
"እኔ እረፍት እፈልጋለሁ"
"እኔ [ስሜትዎን ይግለጹ]" የሚሉትን በመጠቀም ለቤተሰብ ፍላጎትን መናገር።
የግል ተሞክሮዎችን ማካፈል በቤተሰብ አባላት መካከል መተሳሰብን እና መግባባትን ያሳድጋል። ግለሰቡ ብቸኝነት እንዳይሰማው ችግሩን በመደበቅ የበለጠ እንዳይጎዳ ይረዳል።
በአንድ የቤተሰብ አባል የችግር ጊዜ ሞራል በመስጠት ትዕግሥትን ማሳየት ለሁለቱም ወገኖች ወሳኝ ነው። ስሜቶች በሚገለጹበት እና በሚስተናገዱበት ወቅት፣ የራስን የውስጣዊ ስሜት ትግል እያስተዋሉ፣ እያጤኑ፣ እያረሙ እናም እየተቆጣጠሩ በትዕግሥት ከቤተሰብ ጋራ አብሮ በመስራት መቆየት ለግልም የት ልቅ እድገት እና ለራስን የአይምሮ አሰራር እና ውስጣዊ ስሜትን የመቆጣጠር ብቃት (self-regulation) ትልቁ መሠረት ነው።
ፍቅር ሰላም ከናንተ አይለያችሁ።
ኤሚ በላይ ዘለቀ።