የአልኮል መጠጥ በጭንቀት፣በውጥረት ወቅት በአእምሮ ደህንነት ላይ ያለው ተፅዕኖ

ይህ በመንፈስ ውጥረት ወቅት አልኮልን መውሰብ፣ በአእምሮ ጤና ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ የሚገልጽ በጣም ትንሽ መረጃ ነው፦

በውጥረት የአይምሮአዊ (Stress) ወቅት በአልኮል መጠጥ ማስወገድ በጣም ወሳኝ ሲሆን፣ በአጠቃላይ እለታዊውንም ፍጆታን እና በአእምሮ ደህንነት መካከል ያለውን ግንኙነት መረዳት የተሻለ ውሳኔ ለማድረግ ወሳኝ የግል ጠቃሚ የሆኑስ፣ መክትል ያለብን ነስርአቶች ናቸው።

አልኮል በውጥረት ላይ የሚያሳድራቸው ተፅዕኖዎች

  • ጊዜያዊ እፎይታ፦ ብዙ ሰዎች ከውጥረት ፈጣን እፎይታን ለማግኘት ወደ አልኮል ዘወር ይላሉ። አልኮል የመዝናናት ስሜትን ሊፈጥር ቢችልም፣ ይህ ስሜት ግን አብዛኛውን ጊዜ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነው።

  • የጭንቀት መጨመር፦ አልኮል መጀመሪያ ላይ ውጥረትን የሚያለሰልስ፣ ያስጨንቀንን ለጭር ሰአት አእንድረሳው ቢችልም፣ በጊዜ ሂደት ግን ለከፍተኛ ጭንቀት (Anxiety) ሊዳርግ ይችላል። ይህ ተቃርኖ የአእምሮ ጤና ችግሮችን ከማቃለል ይልቅ እንዲባባሱ ያጋደርጋል። ግለሰቡም ያለመጠጥ ችግሮችን ጋፍትጥ ያለመቻል ውስጥ ይከተውና፣ ወደ ቀስበቅስ አዳጊ የአይምሮ መዛባት ይዳርገዋል።

  • #የአይምሮ ደስታው የተረበሸ፣ የተጨነቀ ግለሰብ፣ የሰላሚዊ በስሜቱ ተመልሶ እስኪሰማው ድረስ ከአልኮል ይራቅ።

  • ደስታውንም ይዞ የሚጥጣ፣ፍጆታውን እና የአእምሮ ደህንነቱን በሚመጥን መልኩ ተቆጣጥሮ ቀስ እያለ ይጠጣ።

የረጅም ጊዜ መዘዞች

  • የሱስ ተጋላጭነት፦ ውጥረትን ለመቋቋም አልኮልን ደጋግሞ መጠቀም ለሱስ ሊዳርግ ይችላል። ይህ የሱስ ጥገኝነት መሆን የግለሰቡን ተፈጥሮአዊ የሆነ የውጥረትእና የጭንቀት ስሜቶችን መቆጣጠሪያ ሆርሞኖች በተፈጥሮአቸው መንገድ እንዳያመነጩ የሚያደናቅፍና፣አጠቃላይ የአእምሮ ጤናን በፈጥንት የሚያባብስ ይሆናል።

  • የማሰቢያ ችሎታ መዳከም፦ አልኮልን ለረጅም ጊዜ አዘውትሮ መጠጣት የግለሰቡን አእምሮ የማሰቢያ ችሎታ መቀነስ (Cognitive decline) ሊዳርግ ይችላል። ይህ መዳከም በውሳኔ አሰጣጥ እና በስሜት ቁጥጥር ላይ ተፅዕኖ በማሳደር የውጥረት ምላሽን ይበልጥ ያወሳስበዋል።

ጤናማ አማራጮች

  1. የንቃት (Mindfulness) ልምምዶች፦ ከስልክ፣ከጫጫታ ፍጽሞ ንጻ የሆኑ የተመሰጠ እምነታዊ ጸሎቶችን በተደላደለ ቦታ ሆኖ ለትንሽ ደቂቃ ብቻ በተመስጦ ብቻ በየቀኑ ማሳለፍ አይምሮ ወደቀድሞው ጥንካሬ እንዲመለስ ግዜ ይሰመዋል፣

  2. የራስን የአይምሮ ንቃት በየቀኑ መገምገም፣ ማሻሻል፣አሁን ባሉበት ወቅታው ሃላፊንት፣ ሁኔታ ብቻ ላይ ትኩረት ማድረግን መልመድ ከአልኮል የጎንዮሽ ጉዳቶች በጸዳ መልኩ የመንፈስ ውጥረትን ለመቆጣጠር መጀመር።

  3. አካላዊ እንቅስቃሴ፦ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ውጥረትን ለመቀነስ እና የአእምሮ ደህንነትን ለማሻሻል እጅግ በጣም ጠቃሚ የተረጋገጠ ዘዴ ነው።

  4. ማህበራዊ ድጋፍ፦ ጥሩ ምግባራት ካላቸው ሰዎች ጋራ የድጋፍ መረብ መገንባት፣ የሚያዋዩትን ሰው ጠቃሚ እርዳታ እና መክሮችን በተግባር ማዋል፣ ጤናማ የሆኑ የውጥረት መቋቋሚያ መንገዶችን ለማግኘት አማካሪን እርዳታ ማኘት ወደ ቋሚ የህመም ማስታግሻ መድሀኒት ውስጥ እንዳይሸ ጋገሩ ይረዳል።

ባጠቃላይ፣ አልኮል ለውጥረት ፈጣን መፍትሄ ቢመስልም፣ የረጅም ጊዜ ተፅዕኖው ግን ለአእምሮ ደህንነት ጎጂ ሊሆን ይችላል። ዘላቂ የሆነ አጠቃላይ ጤናን ለመጠበቅ ጤናማ አማራጮችን መፈለግ አስፈላጊ ነው። መቆጣጠር ያልቻልነውን ጭንቀት ሊረዳን ወደሚችል አቋም ሂዶ እርዳታን ማግኝትም አዋቂነት ነው።

ፍቅር፣ሰላም ለሁላችሁም ይሁን።

ኤሚ በላይ ዘለቀ።

Next
Next

የሐበሻ ስደተኛ ቤተሰቦች እና የልጆች የአእምሮ ጤና: